ሚያዝያ 2013 ዓ.ም መጨረሻ በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተመረቀው የሞጆ- ሀዋሳ የመንገድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የሞጆ- ባቱ የክፍያ  መንገድ ከመስከረም 10/2014 ዓ.ም  3 ሰዓት ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አስታወቀ ፡፡

ሚያዝያ 2013 ዓ.ም መጨረሻ በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተመረቀው የሞጆ- ሀዋሳ የመንገድ ፕሮጀክት አካል የሆነው የሞጆ- ባቱ የክፍያ  መንገድ ከመስከረም 10/2014 ዓ.ም  3 ሰዓት ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አስታወቀ ፡፡

በሀገራችን የክፍያ መንገድ ታሪክ ሶስተኛ የሆነው እና 92 ኪ.ሜ የሚሸፍነው የሞጆ- ባቱ የክፍያ መንገድ   አስፈላጊ የክፍያ ማከናወኛ ስርዓት ተሟልቶለት ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙስጠፋ አባሲመል  እንዳስታወቁት 5  የክፍያ ጣቢያዎች (ሞጆ፣ ቆቃ፣ቦቴ፣መቂ እና ባቱ) ያሉትን ጣቢያዎች የክፍያ መንገድ አገልግሎት ለማስጀመር የመክፈያ ማሽኖች ተከላ፣ የታሪፍ ዝግጅት፣ የሠራተኞች ቅጥርና ስልጠና፣ የተለያዩ ግብዓቶችን የማሟላት እንዲሁም አስተዳደራዊ ስራዎች ከመሰራታቸው ጎን ለጎን  ከአከባቢው ማህረሰብና ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት ለመስራት በየደረጃው ውይይት መካሄዱን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ

ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!