የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2014 ዓ.ም አፈጻጸም፣የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ እንዲሁም ወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አደረገ ፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ እንዲሁም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የተቋሙ ሰራተኞች እና ኃላፊዎች በተገኙበት ዉይይት አካሂዷል፡፡

የኢንተርፕራይዙ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙስጠፋ አባሲመል እንደገለፁት ተቋሙ ባሳለፍነዉ የበጀት ዓመት ያስመዘገበዉ ዉጤት የሁሉም ሰራተኛ ጥረት እንዲሁም የአመራሩ ዉሳኔ ሰጪነት የታከለበት በመሆኑ በቀጣይ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል ያስችል ዘንድ ሰራተኛዉን ለማበረታታት ተመጣጣኝ የቦነስ እና የእርከን ጭማሪ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ዉይይት የተካሄደ ሲሆን ሰራተኛው ሀገራዊ ለውጡን በመገንዘብ እና ለሀገር እድገት ማነቆ የሆኑ አመለካከትና ተግባራትን በመመከት በተሰማራበት ሁሉ ውጤት እንዲያስመዘግብና ሀገሩን እዲያግዝ መልእክት ተላልፏል።