Shopping cart

ETRE

It is known that the Government of Ethiopia is undertaking vast and numerous developmental programs to achieve the Growth and Transformation Plan (GTP) series laid out for the holistic renaissance of the country. The Addis Ababa – Adama Expressway (AAE) is one of the construction mega projects developed as part of GTP-I which is open for traffic and administered by the Ethiopian Toll Roads Enterprise. Other expressways (Modjo-Hawassa and Adama-Awash) are underway and many more are planned for future development and operation in line with the dynamic socio-economic development of Ethiopia.

የሞጆ-ባቱ-ሀዋሳ የክፍያ መንገድ የጋራ የመስክ ጉብኝትና የዝግጁነት ግምገማ ተካሄደ።

  • Home
  • News
  • የሞጆ-ባቱ-ሀዋሳ የክፍያ መንገድ የጋራ የመስክ ጉብኝትና የዝግጁነት ግምገማ ተካሄደ።


================================

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የሥራ አመራሮች ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የፖርትፎሊዮ ዳይሬክተር አቶ መኮንን ጋር በመሆን በሞጆ-ባቱ-ሀዋሳ የክፍያ መንገድ ላይ የጋራ የመስክ ጉብኝትና የዝግጁነት ግምገማ አካሄዱ።

የመስክ ጉብኝቱ ዋና ዓላማ የፕሮጀክቱን ወቅታዊ የሥራ እንቅስቃሴ፣ የአፈጻጸም ደረጃ፣ የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን እና ለአገልግሎት ያለውን ዝግጁነት በቦታው በመመልከት መገምገም ነው።

በጉብኝቱ ወቅት በቅርቡ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ለማድረግ በታቀደው የባቱ-አርሲ ነጌሌ የመንገድ ክፍል ላይ የተከናወኑ የማጠናቀቂያና የፋሲሊቲ ሥራዎች ተጎብኝተዋል። በዚህም ሥራዎቹ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መጠናቀቃቸው የተመለከተ ሲሆን፣ የመንገድ ክፍሉ ወደ አገልግሎት መግባት ለተጠቃሚዎች የተሻለ የጉዞ ምቹነትና ደህንነት ከማስገኘቱም በላይ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር ያለው ፋይዳ ተገምግሟል።

በተመሳሳይ በሞጆ የሚገኘው የትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል (ITS/TOC) የሥራ እንቅስቃሴና የአገልግሎት ዝግጁነት ተመልክቷል። በዚህም ዘመናዊ የትራፊክ ክትትልና ቁጥጥር ሥርዓቶች የትራፊክ ፍሰትን በተቀላጠፈና በአስተማማኝ ሁኔታ ለመምራት፣ የመንገድ ደህንነትን ለማረጋገጥና ለተጠቃሚዎች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያላቸው ሚና በጋራ ተገምግሟል።

ከዚህ በተጨማሪ በቆቃ፣ በቦቴና በመቂ አካባቢዎች እየተገነቡ ያሉ የሶላር ፓነል ሲስተም ፕሮጀክቶችና የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የአፈጻጸም ሁኔታም በቦታው ተመልክቷል። እነዚህ የኃይል መሠረተ ልማቶች የመንገዱን ዘመናዊነትና የአሠራር ቅልጥፍና ከማሳደግ ባሻገር ቀጣይነት ያለውን የኃይል አቅርቦት ለማረጋገጥ ያላቸው አስፈላጊነት ትኩረት ተሰጥቶታል።

የመስክ ጉብኝቱን ተከትሎም በፕሮጀክቱ አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸምና የአገልግሎት ዝግጁነት ላይ ግምገማ ተካሂዷል። በግምገማውም ቀሪ የፋሲሊቲና የማጠናቀቂያ ሥራዎች በአስቸኳይና በተቀናጀ መልኩ እንዲጠናቀቁ፣ መንገዱ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለተጠቃሚዎች ክፍት እንዲሆንና አገልግሎቱን በተሟላ ዝግጁነት እንዲጀምር የሚያስችሉ የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በአጠቃላይ የጋራ የመስክ ጉብኝቱ በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ መካከል ያለውን የሥራ ትብብርና ቅንጅት ይበልጥ ለማጠናከር፣ የፕሮጀክቱን አፈጻጸም በቅርበት ለመከታተልና መንገዱ ለሕዝብ በከፍተኛ ጥራት፣ በደህንነትና በቅልጥፍና የታጀበ አገልግሎት እንዲያቀርብ ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት ያረጋገጠ ነው።

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
“ደኅንነትዎ የክብር ስማችን ነው!!”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked*