Shopping cart

ETRE

It is known that the Government of Ethiopia is undertaking vast and numerous developmental programs to achieve the Growth and Transformation Plan (GTP) series laid out for the holistic renaissance of the country. The Addis Ababa – Adama Expressway (AAE) is one of the construction mega projects developed as part of GTP-I which is open for traffic and administered by the Ethiopian Toll Roads Enterprise. Other expressways (Modjo-Hawassa and Adama-Awash) are underway and many more are planned for future development and operation in line with the dynamic socio-economic development of Ethiopia.

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ተካሄደ።

  • Home
  • Uncategorized
  • የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ተካሄደ።

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በይፋ ተካሄደ። በዚሁ መድረክ ላይ ኢንተርፕራይዙ ባለፈው በጀት ዓመት በሁሉም የሥራ ዘርፎች ካቀደው በላይ ውጤታማ እና የተሳካ ሥራዎችን ማከናወኑ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙስጠፋ አባሲመል እንደገለጹት፤ ተቋሙ ላስመዘገበው ውጤት የሠራተኛው እና የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። አያይዘውም ለቀጣዩ በጀት ዓመት ስኬታማነት ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።

ለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች፦

የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ሥርዓት ማስፋፋት እና ዲጂታላይዜሽን፦ ቀደም ሲል የተጀመረውን የኤሌክትሮኒክስ የመንገድ ክፍያ ሥርዓት (Electronic Toll Collection System) ተጠቃሚ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ። በተለይም ዘመናዊ፣ ፈጣን እና ቀለል ያለ የዲጂታል ክፍያ አማራጮችን ከተለያዩ የቴክኖሎጂ መድረኮች ጋር በማቀናጀት የአገልግሎት ተደራሽነትን ማረጋገጥ።

የትራፊክ ፍሰት አስተዳደር እና የደንበኞች እርካታ፦ በክፍያ መውጫ በሮች ላይ የሚያጋጥሙ የትራፊክ መጨናነቆችን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችል አፋጣኝ መፍትሄ መዘርጋት። ለደንበኞች እንግልት የሌለበት እና አስተማማኝ አገልግሎት በመስጠት የጉዞ ጊዜን መቆጠብ።

የክፍያ መንገዱን ማዘመን እና ማስዋብ፦ የክፍያ መንገዱን ኮሪደር (Corridor) የማስዋብ ሥራ በመሥራት መንገዱን ይበልጥ ዘመናዊ፣ ምቹ እና ጽዱ በማድረግ ለተጠቃሚዎች የተሻለ የትራንስፖርት ተሞክሮ እንዲኖረው ማድረግ።

የአገልግሎት ጥራት እና የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ፦ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም የሥራ ሂደትን ማቀላጠፍ፣ የክፍያ በሮችን አቅም በአግባቡ መምራት እና ተቋማዊ ብቃትን ማሳደግ።

የመንገድ ደህንነት እና የትራፊክ አደጋ መከላከል፦ የደንበኞችን ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት፣ በመንገዶች ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስ የሚያስችሉ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል፤ እንዲሁም የአደጋ መከላከያ እና የድንገተኛ ጊዜ ምላሽ ሥርዓቶችን በማዘመን አስተማማኝ እና ሰላማዊ ጉዞን ማረጋገጥ።

ኢንተርፕራይዙ በ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገበው ስኬት ለቀጣይ ሥራዎች ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር የተገለጸ ሲሆን፣ በተቀመጡት አዳዲስ የትኩረት አቅጣጫዎች መሰረትም በ2019 በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት ለማምጣት ቁርጠኛ መሆኑን መድረኩ አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ

ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked*